No media source currently available
የአውሮፓ ሃገሮች በግልም ሆነ በጋራ ከአፍሪካ ሃገሮች ጋር በመሆን የአሸባሪነትን አደጋ ለመዋጋት በቂ ስራ እንዳልሰሩ ተነገረ። ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በተከፈት የሚዩኒክ የጸጥታ ጉባኤ ላይ አውሮፓውያን ከአፍሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከመሰረቱ መለወጥ እንዳለባቸውም ተጠቁሟል። የአሸባሪነትን ስጋትና አደጋ ሁለቱም ወገኖች በአንድነት ሊገመግሙና ሊረዱት እንደሚገባም ተገልፆአል።