No media source currently available
ሊቀ መንበሩ አቶ ይልቃል ጌትነትና አንድ ሌላ ከፍተኛ አመራር እንዲሰናበቱ የጠየቀው የሰማያዊ ፓርቲ የሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ውሳኔ፤ በፓርቲው የኦዲትና ቁጥጥር ኮምሽን እየታየ ነው። የኮምሽኑ ሊቀ መንበር አቶ አበራ ገብሩ ለአሜሪካ ድምጽ እንዳስረዱት አቶ ይልቃል ከፍተኛ ቅሬታ፤ ሌላ አንድ የአመራር አባል ደግሞ አቤቱታ አቅርበዋል።