No media source currently available
የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት ምክትል ሊቀ-መንበርና ሌሎች ሁለት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስ ውለው ዛሬ አዋሳ መግባታቸው ታወቀ። ታሳሪዎቹ ላለፉት አምስት ቀናት ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ ያደረሰን ዘገባ ጠቁሟል። የዞኑ ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት ስልጣን ስለሌለው ታሳሪዎቹን ፍርድ ቤት ለማቅረብ እንዳልቻለ ፖሊስ ይገልጻል።