No media source currently available
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈው ሳምንት በኮሚኒስቷ ኩባ ያደረጉትን ታሪካዊ ጉብኝት ተከትሎ፥ የቀድሞው የሀገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት ሰጥተዋል። የ 89 ዓመቱ ካስትሮ “El Hermano Obama” ወይም ወንድም ኦባማ በሚል ርዕስ ባቀረቡት በ 1,500 ቃላት የተጻፈ አስተያየታቸው፥ ሚስተር ኦባማ ሐቫና ከተማ ውስጥ ለሕዝብ ባደረጉት ንግግር ላይ አትኩረዋል።