No media source currently available
በኦሮሚያ ክልል ከሚካሄደዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ጋር በተያያዘ ከሃላፊነታቸዉ የተነሱ በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት ቁጥር 300 መድረሱን ምክትል ርእስ መስተዳደሩ አስታወቁ። በክልሉ ከተካሄደዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ጋር በተያያዘ ሃላፊነታቸዉን በአግባቡ አልተወጡም በተባሉ አመራሮች ላይ የሚወሰደዉ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ርእሰ መስተዳደሩ አቶ እሼቱ ደሴ ተናግረዋል።