በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


የኅዳሴ ግድብ ግንባታ
የኅዳሴ ግድብ ግንባታ

አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራምን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ግብጽ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን በሳተላይት እንደምትከታተል አስታወቀች፣ እስላም በኢትዮያ መጠጊያ ባያገኝ ኖሮ በእንጭጩ ይቀጭ ነበር ሲሉ ሼኽ አሕመድ ዐል-ጣይብ ገለጹ፣ በኦሮሚያ የሚካሄድ ተቃውሞ፣ ቦኮ ሐራም መራቡ ተገልጸ የሚትሉን ርእሶች ነው በዛሬው ቅንብራችን የምንመለከተው።

World Tribune የተባለ ድረ-ገጽ ያወጣው ዘገባ ግብጽ የታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለመከታተል አዲስ ሳተላይት የመጠቀም እቅድ እንዳላት ገልጿል። በዛሬው ወር የተላከው ሳተላይት የግድቡን ግንባታና ሌሎች የናየል ወይም የአባይ ወንዝ ምንጮችን ጥራት ያላቸው ፎቶግራፎች በማንሳት ይቆጣጠራል ሲሉ የግብጽ የርቀት ቁጥጥርና የጠፈር ሳይንስ ብሄራዊ ባለስልጣን ምክትል ፕረዚዳንት El-din-El-Nahry ገልጸዋል ይላል ድረ-ገጹ ላይ የወጣው ዘገባ።

ሳተላይቱ የሁለት ወራት የሙከራ ጊዜን ካለፈ በኋላ በመጪው ሰኔ ወር መጀመርያ ሳምንት አከባቢ ስራ ይጀምራል ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚፈጠር ጥሰት ካለና ወደ አለም አቀፍ ሽምግልና የሚያስኬድ ሁኔታ ቢፈጠር በሳተላይቱ በኩል አስተማማኝ መረጃ ይኖረናል ሲሉ የግብጽ ባለስልታኖች እንደተናገሩ World Tribune የተባለው ድር-ገጽ ጠቁሟል።

የግብጹ አል-አሕራም ድረ-ገጽ ደግሞ ታላቁ የዐል-አዝሀር ኢማም ሼኽ አሕመድ ዐል-ታይብ ባለፈው ማክሰኞ በጀርመን ፓርላማ ቀርበው ንግግር ባደረጉበት ወቅት መጀመርያ ላይ ለእስላም እምነት መጠግያ የሰጠው ክርስታያን ሃይማኖት ነው ማለታቸውን ገልጿል።

“አቢሲንያና ማለት ኢትዮጵያና ክርስትያን ንጉስዋ የመጀመርያዎቹን ሙስሊሞች ተቀብሎ ባያስጠጋቸው ኖሮ እስላም ሃይሞኖት ከእንጭጩ ይቀጭ ነበር” ሲሉ ለቡንድስታግ እንዳስረዱ ዐል አሕራም ድረ-ገጽ ጠቅሷል።

የግብጹ ሀይማኖታዊ መሪ የጠቀሱት የእስላም እምነት በመቀበላቸው በሀገራቸው ከገጠማቸው ወከባና ሰቆቃ ሸሽተው በኢትዮጵያ ስለተጠጉት የነብዩ መሐመድ ተከታዮች እንደሆነ የዐል አሕራም ጋዜጣ ድረ-ቀጽ ጨምሮ ገልጿል።

ሌሎች ርእሶችም አሉን። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።

አፍሪቃ በጋዜጦች 03-18-16
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:31 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG