No media source currently available
ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዘ ሕዝባዊ ስብሰባ በቅርቡ ጎንደር ከተማውስጥ ተካሂዷል። በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ተጠቃልሎ የሚገኘው የወልቃይት አካባቢ ሰዎች ተወካዮቻቸውን ሰይመውና የሃምሣ ሺህ ሰው ፊርማ አሰባስበው መካለል ያለብን ወደ ትግራይ ሳይሆን ወደ አማራ ነው ብለው ጥያቄአቸውን ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት ልከው እንደነበር ተዘግቧል።