No media source currently available
በአዲስ አበባና በሌሎችም ከተሞች ያለዉ የዉሃ እጥረት በኤልኒኖ ድርቅና በኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ የተባባሰበት ሁኔታ መኖሩን የዉሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሃይል ሚኒስትር አስታወቁ። ችግሩ የሚታወቅ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሣ እልባት ለመስጠትም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነዉ ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አዲስ አበባ ዉስጥ የተካሄደዉ ዓለም አቀፍ የዉሃ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።