No media source currently available
ባለፈው እሑድ አይቮሪ-ኮስት ዋና ከተማ አቢዣን (Abidjan)ውስጥ የተፈጸመው ግድያ፣ በዚያች አገር የሽብርተኛነት አነስተኛው ጅማሮ ነው ተባለ። በጥቃቱ 21 ሰዎች ተገድለው ሌሎችም ቆስለዋል። መንግሥት፣ ሁለት ወታደሮችና ከአጥቂዎቹ መካከል ደግሞ ስድስቱ መሞታቸውንም አመልክቷል። ከተገደሉት ሲቪሎች መካከል፣ እስካሁን ሁለት ብቻ ናቸው የአይቮሪ-ኮስት ዜጎች አለመሆናቸው የተረጋገጠው።