No media source currently available
ባለፉት አራት ወራት ውስጥ ኦሮምያ ውስጥ በተነሣው ተቃውሞ ምክንያት የተገደለው ሰው ቁጥር 270 ነው ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪዎች አስታውቀዋል። የኢሕአዴግ መንግሥት በቃል የሚገልፀውን በተግባር ማሣየት አለበት ሲሉም የኦፌኮ መሪዎች አሳስበዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችም ካሣ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።