No media source currently available
በኢትዮጵያ የማንነት ጥያቄ የሚያነሱ ክፍሎች ቁጥር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የመጣ ይመስላል። የማንነት ጥያቄ ደግሞ ከአሰፋፈርና ከመሬት ይዞታ ጋር በጥብቅ የተሣሰረ ነው። ይህ ጉዳይ በክልሎች ቅርፅና ይዘት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። ይህ ምናልባት የማንነት ጥያቄ በሚነሣሳቸው አካባቢዎች ሁሉ የሚያጋጥም ላይሆን ይችላል። ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ አቅንተን የወልቃይትን ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በተመለከተ በየጊዜው ስንዘግብ ቆይተናል።