No media source currently available
የወልቃይት ሕዝብ ተወካዮች መሆናቸውን የገለጡ ወገኖች ዛሬ ጥያቄዎቻቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ እንዳቀረቡ ገለጹ። አፈ-ጉባኤው ጥያቄዎቻቸውን ሕገ-መንግስቱ በሚያዘው መሠረት እንደሚመለሱና እነሱም ሕዝቡን እንዲያረጋጉ እንደ ጠየቋቸው ተናገሩ። የኮሚቴው አባላት ጨምረው እንዳመለከቱት፤ በትላንትናው እለት ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ለሰዓታት በቁጥጥር ስር ውለው ቆይተዋል። የዘገባውን ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ፤