No media source currently available
ጥሪውን ያቀረቡት የዩናይትድ ስቴትስ፣ የአውሮፓና የመካከለኛው ምሥራቅ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ትናንት እሑድ ከሊብያ ተቀናቃኝ ኃይሎች ጋራ ኢጣልያ ዋና ከተማ ሮማ ውስጥ ተገናኝተው በተወያዩበት ጊዜ መሆኑም ታውቋል። በዚሁ ወቅት፣ ተፋላሚ ወገኖቹ አገራቸውን ወደ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል አንድ በተ.መ.ድ. የሚሸመገል ብሔራዊ የአንድነት ዕቅድ እንዲያጸድቁ ዲፕሎማቶቹ አሳስበዋቸዋል።