በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕረዚዳንት ኦባማ በአፍሪቃ ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲኖር አድርገዋል ተባለ


Obama Africa Ethiopia
Obama Africa Ethiopia

የፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የአፍሪቃ ጉብኘት የ United States ፕረዚዳንትነትንና የአፍሪቃ ዝርያንነትን አቅፎ የያዘ መበሆኑ ለአፍሪቃውያን ያስተላለፉት መልእክት ለአህጉሪቱ ከመቆርቆርም አንጻር እንደሆን ገልጸው ፕረዚዳንት ኦባማ በአፍሪቃ ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲኖር አድርገዋል ብለዋል ስለአፍሪቃው ጉብኝት እንዲተነትኑልን የጋበዝናቸው ዶክተር አየለ በከሬ።

የፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የአፍሪቃ ጉብኘት የ United States ፕረዚዳንትነትንና የአፍሪቃ ዝርያንነትን አቅፎ የያዘ መበሆኑ ለአፍሪቃውያን ያስተላለፉት መልእክት ለአህጉሪቱ ከመቆርቆርም አንጻር እንደሆነ ስለአፍሪቃው ጉብኝት እንዲተነትኑልን የጋበዝናቸው ዶክተር አየለ በከሬ ባለፈው ሰኞ በቀረበው የመጀመርያ ክፍል ቃለ መጠይቅ መግለጻቸው ይታወሳል።

ከሳቸው በፊት የነበሩት ፐረዚዳንቶች ክሊንተንና ቡሽ ለአፍሪቃ ካደረጉት ጋር ሲነጻጸር ፐረዚዳንት ኦባማ ከሳቸው የተጠበቀውን ያህል አላደርጉም ለሚለው አባባል ደግሞ ከነሱ ጋር ሲወዳዳር ትልቅ ነገር አላደረጉም ለማለት ቢቻልም በአፍሪቃ ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲኖር አድርገዋል ብለዋል።

ዶክተር አየለ በኮርኔል ዩኒቨርሲቲ በአፍሪቃ ጥናት ክፍል ለብዙ አመታት አስተምረዋል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ባህል ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። ያነጋገረቻቸው የአፍሪቃ ነክ ርእሶች አዘጋጅና አቅራቢ አዳነች ፍሰሃየ ናት። ፕረዚዳንት ኦባማ ኢትዮፕያ ውስጥ በልማትና በኢኮኖሚ እድገት ረገድ የታዩትን ውጤቶች አሞግሰዋል። የሰብአዊና የዲሞክራሲ አያይዝ ችግሮችንም ማንሳታቸው ይታወሳል ዶክተር አየለ በፕረዚዳንት ኦባማ አቀራረብ ላይ አስተያየት በመስጠት ይጀመራሉ። ሙሉውን ቃለ-መጠይቅ ያድምጡ።

President Obama -Africa 08-10-15
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:20 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG