በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኢራን ጋር የተደረገው ስምምነት መተግበር ለአለም ደህንነትና ለየኢራናውያ ንየኑሮ መሻሳል እንደሚጠቅም ጆን ኬሪ አስገነዘቡ


Secretary of State John Kerry
Secretary of State John Kerry

ከኢራን ጋር የተደረገውን አለም አቀፍ የኑክሌር ስምምነት በተግባር ላይ ማዋል የአለም ደህንነት በበለጠ እንዲጠበቅና የኢራናውያን የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል ያደርጋል። በዩናይትድ ስቴትስና በኢራን መካከል ሌሎች እድሎች እንዲከፈቱ የማድረግ መሰረትም አለው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል።

Iran - Kerry 7-21-15
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:51 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ጆን ኬሪ ከአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የፋርስ ባሀርሰላጤ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ የዩናትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባላት በኢራንና በአሜሪካ በተመራው የስድስት ሃገሮች ቡድን መካከል የተደረገውን ስምምነት ባያጸድቅ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭትና ጦርነት እንዲባባስ የሚያደርግ መሆኑን እንደሚረዱ እተማመናለሁ ብልዋል።

“ይህን ስምምነት ባናደርግ ኑሮ የኢራኑ አያቶላ እነዚህ ሰዎች ያስገኙት ነገር ስለሌለ ከነሱ ጋር የምንደራደርበት ምክንያት የለም ባሉ ነበር። የስራ ባልደረቦቻችን በኢራን ላይ ማዕቅቦች የተጣሉት ወደ ድርድርና ስምምነት እንድታመራ ለማድረግ ነው እያሉ ማዕቀቡ እንዲቀጥል የሚደግፉበት ምክንያት ምንድነው? አሁን የተገኘውን ስምምነት ባይቀባሉ በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ትልቅ አደጋ ይደቀናል” በማለት ጆን ኬሪ አስገንዝበዋል።

የዩናትድ ስቴስ አስተዳደር ኢራን የታሰሩት አሜሪካውያን እንዲፈቱ መጠየቅን የተካተቱባቸው አጀንዳዎችን ጨምሮ መግፋት ነበረበት የሚሉ ነቀፊታዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል። ጆን ኬሪ ታድያ ሌሎች ነጥቦችንም ጨምረን ቢሆን ኖሮ የትም አንደርስም ነበር ብለዋል።

“ከዚህ በፊትም እንደገለጽነው በኢራንና በአለም ማህበረሰቡ ወይም በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በሚደረገው ድርድር ሌሎች ነጥቦችንም አክለን ቢሆን ኖሮ ለ 10 አመታት ያህል ብንደራደርም እንኳን የትም አንደርስም ነበር። ነጥቡ የኑክሌር ጉዳይ በመሆኑ ከተደረሰው መሻሻል አንጻርም ሲታይ ሌሎች ጉዳዮችን ለማንሳት የሚይስስችለን ጊዜ አልነበረንም”ብለዋል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG