በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


ጋምቤላ
ጋምቤላ

የህንድ የእርሻ መዋዕለ-ነዋይ በኢትዮጵያ፣ የእርሻ ዘርፍ የአፍርቃን እድገት እንደሚያንቀሳቅስ ተገለጸ፣ አፍሪቃውያን የእግር ኳስ ባለስልጣኖች በፊፋ ላይ የሚደረገውን ምርመራ የኢምፐርያሊሶች ደባ አድርገው እንደሚያዩት ታወቀ የሚሉት ርእሶች በዛሬው አፍሪቃ በጋዜጦች ዝግጅታችን ይቀርባሉ።

የ CNN ድረ ገጽ ህንድ 1.2 ቢልዮን ህዝቧን ለመቀለብ የምትረዳ የአፍሪቃ ሃገር በሚል ርእስ ባወጣው ጽሁፍ የህንድ ኩባንያዎች በግርድፍ ግምት 600,000 ሄክታር የሚሆን መሬት በኢትዮጵያ ማግኘታቸውን ከህንድ ቀጥሎ ደግሞ የሳውዲ አረብያ ኩባንያዎች የ 500,000 ሄክታር የእርሻ መሬት ስምምነት መረከባቸውን ገልጿል።

ይሁንና ሰፋፊ መሬት የተረከቡት የመዋዕለ-ነዋይ አፍሳሾች በገቡት ስምምነት መሰረት እንደማይሰሩ CNN ድረ ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ ሲያስረዳ በቅርብ የተደረገው ጥናት ኢንቨርተሮች ከተረከቡት መሬት የእርሻ ስራ የጀመሩት ከ 8 ከመቶ ባነሰ መሬት ላይ መሆኑን ያሳያል ይላል።

Theguardian ድረ-ገጽ በበኩሉ የእርሻ ዘርፍ ለአፍሪቃ የኢኮኖሚ እድገት አንቀሳቀሽ ሞተር ይሆናል በሚል ርእስ በወጣው ጽሁፍ የእርሻ ዘርፍ ከማሊ እስከ ታንዜንያ የኢኮኖሚ እድገት እያስፋፋ እንደሆነ ይጠቁማል።

ኢትዮጵያን፣ ጋናን፣ ቡርኪና ፋሶንና ርዋንዳን በመሳሰሉት ሀገሮች የእርሻ መዋዕለ-ነዋይ ድህነትን በመቀነስ ረገድ ከተገኘው አመርቂ ውጤት ጋር ተሳስሯል። የአለም ባንክ እንደሚለው ኢትዮጵያ እአአ ከ 2000 አም ወዲህ የድህነትን መጠን በ 33 ከመቶ ለመቀነስ የቻለችው በእርሻ ዘርፍ እድገት አንቀሳቃሽነት ነው። ርዋንዳም በተመሳሳይ አሰራር ድህነትን በአጭር ጊዜ በ 45 ከመቶ ለመቀነስ የቻለችው በእርሻ ዘርፍና በተያያዥ ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎትች እድገት ምክንያት እንደሆነ የአለም ባንክ መግለጹን Theguardian ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ዘገባ ጠቅሷል።

ታይም መጽሄት ደግሞ የአፍሪቃ የእግር ኳስ ባለስልጣኖች በፊፋ ማለት በአለም አቀፍ የእገር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ላይ ያነጣጠረውን የሙስና ምርመራ ለምን የኢምፐርያሊስቶ ደባ አድርገው እንደሚያዪት ለማጤን ይሞክራል። ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG