በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


The holotype upper jaw of Australopithecus deyiremeda found in Ethiopia on March 4, 2011.
The holotype upper jaw of Australopithecus deyiremeda found in Ethiopia on March 4, 2011.

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሉሲ ዘር የተለየ አዲስ አይነት የቅድመ-ሰው ቅሪት አካል ተገኘ፣ ኢህአዴግ የሚያሸንፈው ሌላ አማራጭ ባለመኖሩ ነው ተባለ፣ ቤተ-ስራኤሎች እስራኤል ውስጥ ስለሚደርስባቸው አድልዎና ዘረኝነት በሚሉት ርእሶች የቀረቡት ዘገባዎች በዛሬው አፍሪቃ በጋዜጦች ይቀርባሉ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:59 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

Natur የተባለው ስለሳይንሳዊ ግኝቶች የሚዘግብ መጽሄት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሱሲ ወይም ከድንቅነሽ ዘር የተለየ አዲስ የቅድመ-ሰው ቅሪት አካል እንደተገኘ ዘግቧል።

ከሉሲና Australopithecus Afarensis ከተባለው ዘርዋ የተለየ መንጋጋ ያለው Australopithecus deyiremeda የተባለ የቅደመ ሰው ቅሬት አካል ከ 3.4 ሚልዮን አመታት በፊት የሉሲ አይትነቶቹ ቅድመ ሰዎች በኖሩበት ዘመን እዛው አከባቢ የኖሩ ዘመዶችዋ አካል እንደሆነ የሳይንስ ምርምሩ መጽሄ ት ጠቁሟል።

ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ደግሞ ባለፈው እሁድ ስለተካሄደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ሲዘግብ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ለምን እንደሚያሸንፍና ተቃዋሚዎች ለምን ብዙም ቦታ እንደማያገኙ ተንትኗል።

የገዢው ፓርቲ ተወዳዳሪዎች ለምርጫ ቅስቀሳ የተጠቀሙበት በሀገሪቱ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አንስቶ አርሶ አደሮች ከድህነት እንዲወጡ እስከ ማድረግ ባሳየው ጥረት ስኬት አግኝቷል። የአለም ባንክ እንደሚለው በ 11 አመታት ውስጥ የድህነቱ መጠን ከ 44 ከመቶ ወደ 30 ከመቶ እንዲቀንስ አድርጓል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸው ገዢው ፓርቲ በፖለቲካ ምህዳር ላይ ያጠበቀውን ልጓም መሰረት በማድረግ ህዝቡን ለማሳመን ሞክረዋል። የምርጫ ዘመቻቸው ያተኮረውም በከተማዎች ላይ ነበር።

ይሁንና ኢሀደግ በሀገሪቱ የፖለቲካ ድባብ ልዕልና ስላለው በተለይም ከሀገሪቱ 80 ከመቶ ህዝብ በሚኖርበት ገጠሩ ክፍል በግልጽ የሚታይ የበላይነት ቦታ ስላለው ተቃዋሚዎች ለማሸነፍ ያላቸው እድል የጠበበ ነው የሚል እምነት በህዝቡ ዘንድ አድሯል ይላል የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘገባ።

ቤተ-ስራኤሎች እስራኤል ውስጥ ይገጥማቸዋል ስለሚባላው አድልዎና ዘረኝነትም ዘገባ አለን ያጽምጡ።

XS
SM
MD
LG