በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደርግ ከስልጣን የተወገደበትን 24ተኛ ዓመት መሰረት በማድረግ የትግራይ ክልል መንግስት የስኬት መግለጫ አወጣ


አቶ አባይ ወልዱ
አቶ አባይ ወልዱ

የቀድሞው ወታደራዊ መንግስት ደርግ ከስልጣን የተወገድበትን 24ተኛ ዓመት ግንቦት 20’ን ተንተርሶ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ባለፉት ዓመታት ውስጥ አስመዘገብኩ ያላቸውን ለውጦች ጠቅሶ መግለጫ አውጥቷል።

የቀድሞው ወታደራዊ መንግስት ደርግ ከስልጣን የተወገደበትን 24ተኛ ዓመት በአል ግንቦት 20’ን ተንተርሶ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ባለፉት ዓመታት ውስጥ አስመዘገብኩ ያላቸውን ለውጦች ጠቅሶ መግለጫ አውጥቷል።

የክልሉ መንግስት በዛሬው እለት ይፋ ባደረገው በዚህ መግለጫው፥ በኢትዮጵያ በተለይ የዴሞክራስያዊ ስርዓት ግንባታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ግንቦት 16 የተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ምሥክር ነው ብሏል።

መግለጫውን የተከታተለው ዘጋቢያችን ግርማይ ገብሩ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የተቃዋሚ ፓርቲ ዓረና-መድረክን ምላሽ አግኝቷል።

የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊው አቶ ዓንዶም ገብረስላሴ በሰነዘሩት አስተያየት “ዘንድሮ የተካሄደው ምርጫ ይልቁንም በኢትዮጵያ ተጀምሮ የነበረውን የዴሞክራሲ ጭላንጭል ያጨለመ ነው፤” ብለውታል። ሙሉ ዘገባው ቀጥሎ ይቀርባል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG