በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


"አፍሪቃ በጋዜጦች" ዛሬ ከሚመለከታቸው ነጥቦች መካከል “የኢትዮጵያ የታፈነ ፕረስ” የሚለው ርዕሰ-አንቀጽና የተሰጠው ምላሽ እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስ ኢቦላን ለመታገል ተልከው የነበሩትን ወታደሮችዋን እንደመትመልስ አስታወቀች የሚሉት ይገኑባቸዋል።

ባለፈው ሰኞ የወጣው የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ርእሰ-አንቀጽ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ልማት ያላት ተወዳጅነት እንዳለ ሆኖ በሚሰደዱት ጋዜጠኞች ብዛት ከኢራን ቀጥላ በአለም የሁለተኛነትን ቦታ ይዛለች ይላል።

ሁማን ራይትስ ዋች የተባለው የሰብአዊ መብት ድርጅት ባወጣው አዲስ ዘገባ መሰረት በአምስት አመታት ውስጥ ቢያንስ 60 የሚሆኑ ጋዜጠኞች ከሀገሪቱ ሸሽተው ወጥተዋል። ባለፈው አመት የወጡት 30 ጋዜጠኞችን ያቅፋል። በትንሹ 19 የሚሆኑት ጋዜጠኞች ደግሞ ታስረዋል። 22 የሚሆኑት የወንጀል ክስ ይጠብቅቸዋል። መንግስት አምስት መጽሄቶችንና አንድ ጋዜጣን ዘግቷል ሲል ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ጠቅሷል።

በ United States የኢትዮጵያ ኤምባሲ የህዝባዊ ዲፕሎማሲና የኮሙኒኬሽንስ ካውንስለር አቶ ተስፋየ ወልዴ “የኢትዮጵያ መንግስት ተግባር መላ ዜጎቹን ከአደጋ መጠበቅ ነው በሚል ርእስ ለዋሽንግተን ፖስቱ ርዕሰ አንቀጽ ምላሽ ሰጥተዋል።

እአአ የካቲት 9 ቀን (ባለፈው ሰኞ ማለት ነው) “የኢትዮጵያው የታፈነ ፕረስ” በሚል ርእስ የወጣው ርእሰ አንቀጽ ኢትዮጵያን ተቃውሞ የሚያንጸባርቅ ሚድያን የምታዋክብ የፖለቲካ ጭቆና የሰፈነባት ሀገር አድርጎ አቅርቧታል። ይህ ከእውነት የራቀ ነው። መንግስት በህግና ስርአት ላይ የተመሰረተ ህብረተሰብ በመገንባትና በኢኮኖሚ ልማት ላይ አትኩሮ ለ 24 ሰአታት ሲሰራ ቆይቷል ይላል። ኢትዮጵያ ውስጥ እያበበ የሄደው አዲስ ህገ-መንግስታዊ ስርአት የህዝቡ ፍላጎት ነጸብራቅ ነው። መንግስት የሀገሪቱን ህገ-መንግስታዊ ስርአት ከማንኛውም አይነት የማናጋት ተግባር የመጠበቅ ግዴታ አለበት ይላል ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ርዕሰ-አንቀጽ የተሰጠው ምላሽ። ዝርዝሩን ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG