የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ትላንት Bata, Equatorial Guinea አስጨኳይ ስብሰባ ጠርቶ፥ በሞሪሽየሱ ዳኛ ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል።
ዳኛ Seechurn Rajindrapasard ቱኒዝያና ኢኳቶሪያል ጊኒን ባጫወቱበት ወቅት ባግባቡ ተቆጣጥረው አልመሩም ተብለው የስድስት ወር እገዳ ተጥሎባቸዋል። የ 2015 የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ተልዕኳቸውንም ሠርዟል።
በሌላ በኩል የቱኒዝያ ተጫዋቾችም ሜዳ ውስጥ ዳኛውን ለመደብደብ በመጋበዛቸውና መልበሻ ክፍል ውስጥ ንብረት በማውደማቸው እንዲሁም በ CAF ላይ ላሳዩት ንቀትና ዘለፋ ፌዴሬሽኑን በ $50 ሺህ ዶላር ቀጥቷል።
አስተናጋጅ ኢኳቶሪያል ጊኒም በጸጥታ ማስከበር መላላት ተወቅሳለች ውድድሮቹ በሰላም ማለቃቸውን እንድታረጋግጥ ማሳሰብያና የ5 ሺህ ዶላር ቅጣት ሰጥቷታል