በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


ፋርም አፍሪቃ
ፋርም አፍሪቃ

በዛሬው ፕሮግራማችን ፋርም አፍሪካ በድህነት ለሚኖሩ ሴቶች የሚሰጠው እርዳታና የኬንያ ትንንሽ ልጆች በባለሀብቶች ሊወሰድ የነብረውን መጫወቻ ቦታ አስመለሱ የሚሉት ርእሶች ይኖሩናል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


የረድኤቱ ድርጅት በኢትዮጵያ የሚያቀርባቸው ፍየሎችና ንቦች የአርሶ አደሮችን ኑሮ እየለወኡ እንደሆነ The guardian ጋዜጣ ድረ-ገጽ ገልጿል።

Farm Africa የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ዝር ባላለበት የትግራይ ደጋማ አከባቢዎች የሚኖሩት ሰዎች ራሳቸውን እንዲችሉ ለመርዳት በሚያደርገው ጥረት ተጠቃሚ የሆኑት ባለቤታቸው የሞቱባቸው ለታይ ገብረ-ሚካኤል ተጠቃሽ ሆነዋል።

ልጆቻቸውን የሚመግቡት በቀን ሁለቴ ብቻ ነበር። Farm Africa ከተባለው፣አለም አቀፍ የረድኤት ድርጅት፣ ሶስት ፍየሎች ካገኙ በኋላ ግን፣ ልጆቻቸውን በቀን ሶስት ጊዜ ከመመገብ አልፈው፣ መክሰስም ይሰጥዋቸዋል። ሶስቱ ፍየሎች እያንዳንዳቸው ሁለት፣ ሁለት በመውለዳቸውም፣ የዘጠኝ ፍየል ባለቤት ሆኑ።

በኬንያ ናይሮቢ ደግሞ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ናይሮቢ የሚገኘው የመጫወቻ ቦታቸው ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በግል ባለሀብት መወሰዱን በመቃወማቸው ፖሊሶች እምባ አስመጪ ጋዝ ስለተኮሱባቸው በመላ ከተማይቱና በማህበረ-ሰባዊ ሚድያ ቁጣ አስነሳ።

ተማሪዎቹ ተቃውሞ ባካሄዱበት ማግስት የኬንያው ፕረዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በልጆቹ ላይ እምባ አስመጪ ጋዝ መተኮሱን አውግዘው በተግባሩ ላይ የተሳተፉትን ከፈተኝ መኮንን ከስራ አግደዋል። ቦታውም ለትምህርት ቤቱ ተመልሷል።

XS
SM
MD
LG