በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት አደርጋለሁ አለ


አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ባለው ዘመቻ የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት አደርጋለሁ አለ። ፓርቲው በአሁኑ ጊዜ በመላ የሀገሪቱ ክፍሎች መዋቅሩን መዘርጋቱናን በየትኛውም ደረጃ የምክር ቤት እጩዎችን ለማቅረብ እንደሚችል ገልጿል።

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሚቀጥሉት የምርጫ ወራት በሚልዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን እናደርጋለን ሲል ዛሬ ረፋዱ ላይ በጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ላይ ባሰራጨው ጽሁፍ ግልጽ አድርጓል።

ከዚህ ቀደም ፓርቲው ያካሄዳቸውን የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነትና የሚልዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ንቅናቄዎች አስታውሶ በተለይ በመጀመርያው እንቅስቃሴ የፈለገውን ውጤት እንዳገኘ የፓርቲው የውጭ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ አብራርተዋል።

ሶስተኛውና የመጨረሻው የአንድነቶች የሚልዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴ ይኸው የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነትና ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል መሆኑንም የጽሁፉ መግለጫ ይጠቁማል።

አንድነት በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር ለማምጣት ላቀደው ዋነኛ የትግል ምዕራፍ በሀገራችን እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ፓርቲውን በአበላነትና በደጋፊነት በመቀላቀል የለውጡ አካል እንዲሆኑ የሚያደርግ ተደራጅ 2007 ለለውጥ የሚል ሰፊ የማደረጀትና የቅስቀሳ ዘመቻ ለማካሄድ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ገልጿል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:14 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


አስተያየቶችን ይዩ (6)

XS
SM
MD
LG