History Channel የተባለ ስለታሪክ የሚግልጽ የአሜሪካ ቴሌቪዥን ስርጭት ድረ-ገጽ ዝነኛዋ “ሉሲ” ወይም ድንቅ ነሽ ስለተገኘችበት አርባኛ አመት ጽሁፍ አቅርቧል።
የሰው ልጅ አመጣጥ ታሪክ ተመራማሪ Donald Johnson እና የድህረ-ምረቃ ተማሪ Tom Gray ከአርባ አመታት በፊት በኢትዮጵያው የአፋር ክልል የቅድመ-ሰው ቅሪት አካላት ፍለጋ ሲዘዋወሩ ባለፈው ማክሰኞ በዋለው እአአ ህዳር 24 ቀን 1974 አም. አንድ ነገር አደናቀፋቸው። የ ያደናቀፋቸው ነገርም ከዚያ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የዝንጀሮ አምሳያ ያለው የቅሬት አካል ክፍል ነበር።
ያቅሪት አካል ታድያ ውሎ አድሮ የ 3.2 ሚልዮን አመት እድሜ ያላት ”Australopithecus afarensis” የተባለች ከቅድመ-ሰው የዘር ግንድ አንዷ እንደሆነች ለማወቅ ተቻለ ይላል ሂስትሪ ጽረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ። ሉሲ የተገኝበት ሐዳር ክፍል የጥንት ቅድመ ሰው ቅሬት አካል በብዛት የሚኝበት አከባቢ ነው። ሌሎች ርእሶችም አሉንና ያድምጡ።