theguardian ጋዜጣ ድረ-ገጽ በያዝነው ሳምንት ባወጣው ጽሁፍ ኤርትራ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች በፕረዚዳንት ኢሳያስ ላይ ጫና እያሳደሩ ነው ይላል። ኤርትራ ከአፍሪቃ አስከፊ ጭቆና ያለባት ዝግ ሃገር ናት። በሀገሪቱ የውጭ ጋዜጠኞች የሉም። አለም አቀፍ ሚድያም ለሀገሪቱ ተደራሽነት የለውም ይላል ጽሁፉ።
በዚህ ሁኔታ ታድያ ሁለት የተቃዋሚ ቡድኖች አባላት ከጸጥታ አንጻር አስተማማኝ በሆነ ግንኑነት በኩል በሀገሪቱ ስላለው ሁኔታ ለጋርዲያን ጋዜጣ አስረድተዋል። ውሀን፣ የኤለክትሪክ መብራትንና ነደጅ ዘይትን የመሳሰሉት መሰረታዊ አቅርቦቶች ጠፍተዋል። የምግብ ዋጋም በጣም ውድ በመሆኑ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች እንኳን ሳይቀሩ በቂ ምግብ አያገኙም ሲሉ ለጋርዲያን ጋዜጣ እንደተናገሩ ዘገባው ጠቁሟል።
ተቃዋሚዎቹ ቀጥለውም አስመራ ውስጥ ውጥረት ሰፍኗል። በኤርትራ የሚረዱት ደምሂት በሚል ስያሜ የሚታወቁት የትግራይ ህዝባዊ ዲምክራስያዊ ንቅናቄ አባላት “ቅጥረኞች” በጭነት መኪናዎች ሆነው አስማራን ከበዋል ይላል theguardian ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ።
በምዕራብ አፍሪቃ የተዛመተው ኢቦላ ሁኔታ አዎንታዊ ለውጥ የሚታይበት እንደሚመስል Wellcome Trust የተባለው ለኢቦላ የሙከራ መድሀኒቶችና ክትባቶች ገንዘብ የሚያቀርበው ተቋም ስረ አስክያጅ መናገራቸውን theguardian ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ ያወሳል። ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ።