በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተበላ! ጀርመን በላችው!


የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ
የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ

ጎ............ል! ጀርመን 1 አርጀንቲና 0 - ሃያኛው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ ተጠናቀቀ፡፡ ጀርመን አርጀንቲናን በፍፃሜ ግጥሚያ ለሁለተኛ ጊዜ ድል ነሣች፡፡

ማሪዮ ግዮትዜ
ማሪዮ ግዮትዜ

ጀርመን አርጀንቲናን በፍፃሜ ግጥሚያ ለሁለተኛ ጊዜ ድል ነሣች፡፡ ጨዋታው በተጨማሪ የጨዋታ ጊዜ በተቆጠረች ግብ አንድ ለባዶ አለቀ፡፡

በሪዮ ዴ ጃኔይሮው ማራካና ስታዲየም የተካሄደው ጠንካራ ሊባል የሚችል ትንቅንቅ የታየበት ጨዋታ ዋናው የግጥሚያ ጊዜ /ዘጠና ደቂቃው/ የተጠናቀቀው፣ ብዙ የግብ አጋጣሚዎች ተፈጥረው የነበረ ቢሆንም፣ ያለምንም ግብ ባዶ ለባዶ በሆነ ውጤት ነበር፡፡

ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ዘልቆ 112 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ ላይ 19 ቁጥር ለብሶ የሚጫወተው ማሪዮ ግዮትዘ በድንቅ አስተላለፍ የአርጀንቲናን በረኛ አሳልፎ መረብ ላይ ያስቀመጣት ኳስ የጨዋታውም ለብርቱው የጀርመን ቡድንም በዚህ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም ግብ ሆነች፡፡

ጎ............................ል! ጀርመን የዓለም ዋንጫን ለአራተኛ ጊዜ ወሰደች፡፡

በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ታሪክ ጀርመን 4 ጊዜ አሸንፋ አምስት ጊዜ ያሸነፈችውን ብራዚልን እየተከተለች ነች፡፡

በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ታሪክ ውስጥ እአአ በ1954 ዓ.ም ልክ የዛሬ ስድሣ ዓመት ስዊትዘርላንድ አዘጋጅታው በነበረው 5ኛው የዓለም ዋንጫ ላይ ጀርመን ሃንጋሪን 3 ለ 2 አሸንፋ የመጀመሪያውን ዋንጫዋን ወስዳለች፡፡

ከዚያም እአአ በ1974 ዓ.ም እራሷ /የያኔዋ ምዕራብ ጀርመን/ አዘጋጅታው በነበረው 10ኛው የዓለም ዋንጫ ላይ ለፍፃሜ ከሆላንድ ጋር ተገናኝታ 2 ለ 1 አሸነፈች፡፡

እአአ በ1990 ዓ.ም /የዛሬ 24 ዓመት/ ጣልያን ባዘጋጀችው 14ኛው የዓለም ዋንጫ ልክ እንደዛሬው ጀርመንና አርጀንቲና ተገናኝተው፤ ልክ እንደዛሬው ጀርመን አርጀንቲናን 1 ለ 0 አሸንፋ ዋንጫውን አስቀረች፡፡

ዛሬ፣ ዕሁድ - ሐምሌ 6/2006 ዓ.ም /በኢት.የዘ.አቆ/ የሪዮ ዴ ጃኔሮው ማራካና ስታዲየም ላይ ጀርመን የዛሬ ሃያ አራት ዓመቱን ታሪክ ደገመች፡፡

የማርዮ ግዮትዘን ጎል ለማየት ከታች የተቀመጠውን ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ፤
http://www.espnfc.com/video/latest-videos/600/video/1948633?&ex_cid=espnapi_affiliate_Google_World_Cup_Video

የጀርመኑ ባስቲያን ሽቫይንሽታይገር ከአርጀንቲናዎቹ ሉካስ ቢህሊያና ሊዮኔል ሜሲ ጋር የነበረው ፍጥጫ - ሪዮ ዴ ጃኔይሮ - ማራካና ስታዲየም፤ ዕሁድ - ሐምሌ - 6/2006 ዓም
XS
SM
MD
LG