ዋሽንግተን ዲሲ —
“ወንድምሕ የት ነው?” በሚል ጥያቄ ርእስ አራት የኤርትራ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ያቀረቡት ባለ 33 ገጽ ጽሁፍ ከሚያነሳቸው አበይት ነጥቦች መካከል የኤርትራውያን በብዛት ከሀገር መሰደድና ምክንያቱ፣ የህግ የበላይነት ጥያቄ፣ በሃገሪቱ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የትምህርት ይዘት፣ እስረኞች ሰብአዊነት በተላበሰ መንገድ እንዲያዙና በተቻለ ፍጥነት የፍርድ ሂደት እንዲገኙ የሚጠይቁና ሌሎች በርካታ ነጥቦች ይገኙባቸዋል።
ጽሁፉ ስለ ሀገሪቱ ህዝብ ባህሪ ሲገልጽም “ሀገራችን ሞልቶ የፈሰሰ ወይም የተትረፈረፈ የተፈጥሮ ሃብት ባይኖራትም እንኳን ፈሪሀ እግዜብሄር ያደረበት በሀይሞኖትና በዘር ሳይለያይ ብዝሀነትን ጸጋና በረከት አድርጎ በመቀበል ተከባብሮ የሚኖር ሰላማዊ ህዝብ ስላለን አምላካችንን ማመስገን ይገባናል” ይላል። ሙሉውን ዘገባ ያድምጡ።