ዋሽንግተን ዲሲ —
New York Times ጋዜጣ በግብጽ ስላለው ሁኔታ ሲዘግብ ግብጽ በተካሄደ ነጻ ምርጫ ተመርጠው የነበሩት መሐመድ ሞርሲ ጄኔራል ዐብደል-ፋታሕ ዐል-ሲሲን ለመከላከያ ሚኒስትርነት ሲሾሙ የሀገሪቱ ወታደራዊ ሀይል በፖለቲካ ውስጥ እንዳይገባ ለማድረግና ለሲቪል ዲሞክራሲ ቦታ እንደሚለቁ ቃል ገብተው ነበር ይላል።
ከአንድ አመት በኋላ ግን ጄኔራል ሲሲ ወታደራዊው ሃይል የህዝቡን ጥያቄ ነው የመለሰው በሚል የቀድሞውን ፕረዚዳንት ሞርሲን ከስልጣን አስወገዱ። ከሶስት ሳምንታት በኋላ ደግሞ የሞርሲ መሰረት የሆነውን ሙስሊም ወንድማምችነትን ለመምታት ህዝቡ እንዲደግፋቸው ጥሪ አቀረቡ።
ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በአንጻሩ በቱኒዥያ ከአረብ ሃገሮች ህዝባዊ መነሳሳት በኋላ በህዝብ የተመረጠው እስላማዊ ኢናሕዳ ፓርቲ
ባለፈው ማክሰኞ ስልጣኑን ለእምባ ጠባቂ መንግስት እንዳስረከብ ገልጿል።
የኢናሕዳ መንግስት እያቆጥቆጠ በመሄድ ላይ ያለውን አሸባሪነት ለመግታት
አልቻለም። እየዳሸቀ በመሄድ ላይ ያለውን ኢኮኖሚንም ሊያቃና አልቻለም በሚል ቢነቀፍም በቱኒዥያ ፖለቲካ ውስጥ ቦታ እንደሚኖረው ማራጋገጫ
ተስጥቶታል ይላል ጋዜጣው።