ዋሽንግተን ዲሲ —
USA Today የተባለው የአሜሪካ ጋዜጣ በለንዶን ሂትሮ አይሮፕላን ማረፍያ ላይ እንዳለ ቃጠሎ ደርሶበት የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 787 ድሪምላይነር አይሮፕላን አገልግሎት ጀምሯል ይላል።
አይሮፕላኑን የጠገነው ቦይንግ እንደሆነና የጥገናውና የመልሶ ማስተካከሉ ስራ ሁለት ወራት እንደፈጀ ጋዜጣው ጠቁሟል። አይሮፕላኑ ከ 19 ቀናት በፊት ከጀርመን ፍራክፈርት ወደ አዲስ አበባ እንደበረረ USA Today ላይ የወጣው ዘገባ ገልጿል።
ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ የወጣ ዘገባ ደግሞ ከሳውዲ አረብያ ስለ ወጡት ኢትዮጵያውያን ሲጽፍ መሃመድ ጀማል የተባለ ወጣት ኮሌጅ ገብቶ ከወጣ በኋላ በአብዛኛው በእግሩ በጂቡቲና በየመን በኩል ትጉዞ ሳውዲ አረብያ እንደገባ አዛም በዘበኛነትና በአስተናጋጅነት እንደሰራ ገልጿል።
ኑሮው ቀላል ባይሆንም ክፍያው ጥሩ እንደነበረ መሐመድ ጀማል አውስቷል። ሳውዲ አረብየ ህጋዊ ፈቃድ የሌልላቸውን የውጭ ሃገራት ተውላጆችን ከሀገርዋ ለማስወጣት ባደረገችው ውሳኔ መሰረት 150,000 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። እነዚህ ሰዎች ወደ ሀገራቸው ብዙ ገንዘብ ይልኩ የነበሩ ናቸው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአለም በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ጋር የሚፈረጅ ቢሆንም አሁንም ሀገሪቱ በድህነት መፈረጅዋ አልቀረም ይላል ጋዜጣው።ዝርዝር ዝግጅቱን ያድምጡ።