በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


በ United States ደንቨር ኮሎራዶ ሀብተአብ በርሀ ጠማኑ በሚል ስም ለ8 አመታት ያህል በሚቀርባቸው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቀልደኛና ተወዳጅ ተደርጎ ሲታይ የነበረው ሰው፣ “እማውቅህ ይመሰላኛል” የሚሉ ሁለት ቃላት ማንነቱን አጋለጡ። ደብቆት የኖረው ጭካኔ የተመላበት ድርጊቱ ይፋ ሆን ሲል ደንቨር ፖስት የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል።

እአአ ግንቦት 6 ቀን 2011 አም ከሁለት አመታት ተኩል በፊት ማለት ነው፣ ክፍሉ ከተማ የተባለ ኢትዮጵያዊ አውሮራ በተባለው የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ደጃፍ ቆም ብሎ ሳለ ያለፈውን ታሪኩን ለመርሳት ሲሞክር የነበረው ሰው ገጠመውና “እማውቅህ ይመስለኛል” ሲለው አይ አታቀኝም አለ።

በደርጉ አገዛዝ ወቅት በነበረው ቀይ ሽብር ወቅት በከፍተኛ 15 እስረኛው እንደነበረ ሲነግረው“የለም ተሳስተሃል። ምናልባት ወንደሜ ይሆናል” እንዳለው ከተማ መልሶ እረ አንተ ነህ እዛ የነበርከው ሲለው ክፍሉ “አውሬ” የሚለው በከፍተኛ 15 እስር ቤት ብዙ ሰዎች ገደለና አሰቃየ የሚባለው ሰው መንቀጥቀጥ እንደጀመረ ክፍሉ ከተማ በፍድርድ ቤት ቃለ-ምስክርነቱን ሲሰጥ መናገሩን ደንቨር ፖስት የተባለው ጋዜጣ ጠቁሟል። የዚህንና የሌሎቹንም ዝርዝር ይዘት ያድምጡ።
ETHIOPIA-PRESS-REVIEW-1-25-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG