ዋሽንግተን ዲሲ —
The Group of the Nile Basin” የተባለው ቡድን ያቀረበው የጥናት ዘገባ የግብጽን የውሀ አቅርቦት በማረጋገጥ ጉዳይ ላይ ያልታሰቡ ተከታታይ የውጭ ተግዳሮቶች ተደቅነዋል ይላል። የእነዚህ ተግዳሮቶች ምንጮች የኢትዮጵያ መንግስት በብሉ ናየል ወንዝ ላይ አራት ግድቦች ለመገንባት ማቀዱ ነው።
ዋናው አደጋ ግን የኢትዮጵያ መንግስት የግርጌ ተፋሰስ ሀገሮች የሆኑትን ግብጽንና ሱዳንን ሳያማክር የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጀመሩን የሚያመለክተው የአባይ ወንዝ ውሀ የፍሰት አቅጣጫ መቀየሩን ማስታወቁ ነው ይላል ዘገባው። ይህ ተግባርም በአብዛኞቹ ግብጻውያን አመለካከት በመላ መሰረታዊ ህጎችና በአለም አቀፍ ህጎች ላይ በግላጭ የተከፈተ ጥቃት ነው ይላል የጥናት ጽሁፉ።
የጥናቱ ጽሁፍ ኢትዮጵያ ከግብጽና ከሱዳን ጋር የድርድር ስምምነት ላይ እስከምትደርስበት ጊዜ ድረስ የግድቡን ግንባታ ማቆም አለባት ይላል።
በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ የጂኦግራፊ አስተማሪና የጆኦግራፊ ክፍል ሃላፊ አቶ ብርሀኑ በላቸው ግን በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ አለም አቀፍ ህግ የሚባል ነገር የለም ብለዋል። በ1993 አም ሃምሌ 1 ቀን ኢትዮጵያና ግብጽ እየተመካከሩ ለመስራት ካይሮ ላይ የመግባብያ ሰነድ የፈረሙ ቢሆንም ግብጽ ያለ ኢትዮጵያ እውቅና፣ ምክክርና ፈቃድ ሌሎች ፕሮጀክቶች አስፋፍታለች ሲሉም አቶ ብርሀኑ አስገንዝበዋል። ሙሉውን ክፍል ያድምጡ