በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች፥ ሥነ ግጥም፥ ስዕልና ሙዚቃ፤ ጥበብና ጥበበኞች


የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።

ሥነ ግጥም፥ መንገድና የኑሮ ትዝብቶች፤ ቆይታ ከወጣቱ ባለ ቅኔና ደራሲ በእውቀቱ ስዩም ጋር፤“የጥበብና የባህል ውዳሴ፤ የእስክንድር ቦጎሲያን መታሰቢያ፤” ስለ እውቁ ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ህይወትና ሥራ ክብር የተሠናዳ ዝግጅት ማስታወሻ እና ሌሎች ወጎች ከሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ስንቆች ውስጥ ናቸው።

የዛሬ አሥር ዓመት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ሰዓሊ እስክንድር ቦጎሲያን የተደነቀ የሥነ ጥበብ ዘዬና የሙዚቃ ፍቅር፤ የህይወት ዘይቤና ምሳሌ፤ ስለ እርሱ ክብር የተባለውን የጥበብ ቀን በአንጋፋው ገጣሚና ሃያሲ ሰለሞን ደሬሳ እና እንዲሁም በእውቋ ሰዓሊና ገጣሚ ከበደች ተክለአብ ማስታወሻዎች መልከት እናደርጋለን።
XS
SM
MD
LG