በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


ኅዳሴ ግድብ በግንባታ ላይ
ኅዳሴ ግድብ በግንባታ ላይ
ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አሶሼተድ ፕረስን ጠቅሶ ባሰፈረው ዘገባ የኢትዮጵያው መሪ የታላቁን የሕዳሴ ግድብ ግንባታን የሚያቆም ሀይል የለም የሚል መልስ ሰጥተዋል ይላል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ይህን ምላሽ የሰጡት የግብጹ ፕረዚዳንት በአሁኑ ወቅት የአባይን ፍሰት አቅጣጫ እንዲቀየር ያደረገውን $4.2 ቢልዮን ዶላር የሚፈጀውን የኤለክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ለማቆም “አማራጮች ሁሉ ክፍት ናቸው” ካሉ በኋላ ነው ሲል ዘገባው አውስቷል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ በተላለፈው ቃለ መጠይቅ ሲናገሩ “ሁሉም አማራጮች ሲባል ጦርነትንም ያካትታል ማለት ነው። ካላበዱ በስተቀር ያንን አማራጭ ይወስዳሉ የሚል እምነት የለኝም። እንዲህ አይነቱን እያያዝ ትተው ወደ መነጋግሩና መወያየቱ ጉዳይ እንዲያመሩ ጥሪ አደርጋለሁ” ማለታቸውን ጋዜጣው ጠቅሷል።

ሱዳን አራት አለም አቀፍ ጠበብትንም ባቀፈው ቡድን የቀረበውን ዘገባ እንደተቀበለች የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የሱዳን መንግስትና ህዝብ ለድጋፋቸዋና ለጋራ ጥቅም ለመስራት ቁርጠኛ በመሆናቸው ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ ብለዋል ይላላ የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘገባ።
AMH-af-Ethiopia-Press-Review-6-14-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG