በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብጹ ፕረዚዳንት ዛቻና የኢትዮጵያ ምላሽ


ኅዳሴ ግድብ በግንባታ ላይ
ኅዳሴ ግድብ በግንባታ ላይ
የግብጹ ፕረዚዳንት መሐመድ ሞርሲ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሀገራቸው አደጋ ያስከትላል ከሚል እምነት የተነሳ ባደረጉት ንግግር “ሁሉም አማራጭ ክፍት ነው” ብለዋል። ፕረዚዳንቱ ይህን ያሉት ትላንት በቴሌቪዥን ለሀአገሪቱ ህዝብ ባደረጉት ንግግር ነው።

“ማንም በግብጽ የውሀ መብቶች ላይ እጁን እንዲዶል ወይም ጉዳት እንዲያደርስ አንፈቅድም። እኔ እንደ ፕረዚዳንት ጉዳዮን በሚመለከት ሁሉም አይነት አማራጭ ጠረጴዛ ላይ እንደሆነ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ግብጻውያን በአብዮታቸው በኩል ለአለም የሰላም መልእክት እንዳቀረቡ በተደጋጋሚ ተናግረናል። የጦርነት ጥሪ አናደርግም። ነገር ግን በውሀ ጸጥታችንም ሆነ በማንኛውም አይነት ጸጥታችን ላይ ጉዳት እንዲደርስ አንፈቅድም” ብለዋል ፕረዚዳንት ሞርሲ።

“ግብጽ የናየል ስጦታ ከሆነች፣ ናየል የግብጽ ስጦታ ነው” የሚለውን የግብጻውያን ጥቅስንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች በበኩላቸው ግድቡን ከመገንባት ሊያስቆም የሚችል የውስጥም ሆነ የውጭ ሀይል አይኖርም ሲሉ በተደጋጋሚ አስገንዝዋል። ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ የሞርሲን አነጋገር የቀድሞው የግብጽ ፕረዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ አሳዩት ካሉት ”አስመሳይ ወታደራዊ ሃያልነት” ጋር አመሳስለውታል።
AMH-af-Egypt-Ethiopia-Dam-6-11-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:49 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ



“ፕረዚዳንት ሞርሲ የቀድሞው የግብጽ መሪ ተክንውበት ወደ ነበረው አስመሳይ ወታደራዊ ሃያልነት መዝቀጣቸው ያሳዝናል። ፕረዚዳንቱ እጅግ ለተከፋፈለው ህዝብ ፍጆታ እየተናገሩ ነው ቢባል ከእውነት የራቀ አይሆንም" ሲሉ አቶ ጌታቸው ምላሽ ሰጥተዋል።
XS
SM
MD
LG