በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ የአባይ ወንዝ አቅጣጫን በመቀየርዋ ግብጽ የተሰማትን ቅሬታ ለመግለጽ በሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ክፍል ሀላፊ የሆኑት አምባሳደር ዐሊ ሄፍኒ ግብጽ ያሉትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ማሕሙድ ዳርዲርን ባለፈው ረቡዕ እንዳነገገሩ ከግብጽ ጋዜጣ ዐል አሕራም ጋር የተሳሰረው አሕራም ድረ-ገጽ ዘግቧል።

ስለ ጉዳዩ እንዲያጠና የተመሰረተው የጠበበት ኮሚቴ ዘገባውን ከማቅረቡ በፊት ኢትዮጵያ በውጥኑ በመቀጠልዋ የግብጽ ዲፕሎማቶች እንደነቀፉ ድረ-ገጹ ጠቅሷል። ኮሚቴው የኢትዮጵያ የግብጽና የሱዳን ጠብትንም ያቅፋል።

በኢትዮጵያ የግብጽ አምባሳደር መሐመድ ኢድሪስ ባለፈው ማክሰኞ ከአሕራም ድረ-ገጽ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ ግብጽ የሁለቱንም ሃገሮች ጥቅም የሚጠበቅበትና የሚካተትበት መንገድ እየተከተለች ነው። “የኢትዮጵያ ባለስልጣኖችም የግብጽ ጥቅም በማይጎዳበት መንገድ ለመስራት የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ እንጠብቃለን” ማለታቸውን ድረ-ገጹ ጠቁሟል።
AMH-af-Ethiopia-Press-Review-5-31-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG