በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤርትራ 10,000 የፐለቲካ እስረኞች ካለፍርድ እንደተያዙ አምነስቲ ገለጸ


ኤርትራ
ኤርትራ
ዋናው መስሪያ ቤቱ ለንደን የሆነው የሰብአዊ መብት ድርጅት ትላንት ባወጣው አዲስ ዘገባ ኤርትራ እአአ በ 1993 አም ራስዋን የቻለች ሃገር ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ የሀገሪቱ መንግስት በትንሹ 10,000 የፖለቲካ እስረኞችን ይዟል ይላል።

እስረኞቹ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች፣ከሀገሪቱ ሸሽተው ለመውጣት የሞከሩ ሰዎች፣ጋዜጦኞችና በመንግስቱ ተቀባይነት የሌለው ሀይማኖታዊ እምነትን የሚከተሉ ሰዎች ይገኙባቸዋል።

በአምነስቲ የኤርትራን ጉዳይ የሚያጠኑትና የሚከታተሉት Claire Beston እስረኞቹ በሃገሪቱ ዙርይ በሚገኙ ድብቅ ቦታዎች እንደተያዙና ሰቆቃና በደል እንደሚፈጸምባቸው ገልጸዋል።

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ላወጣው ዘገባ ምላሽ መግለጫ አውጥቷል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኤርትራ “በትንሹ 10,000 የፖለቲካ እስረኞችን አስራለች” ያለውን ኤርትራ እንደማትቀበልው ግልጽ ታደርጋለች ይላል መግለጫው።

አምነስቲ በኤርትራ ላይ ያደረሰው የፖለቲካ ጥቃት ፈጽሞ በተጨባጭ ሀቆች አልተረጋገጣም። እስረኞቹ “ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ተይዘዋል” የሚለውም በፈጠራ እንጂ በተአማኒ ማስረጃ የተደገፈ አይደለም ይላል የኤርትራው መግለጫ።
AMH-af-Amnesty-International-Eritrea-5-10-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:59 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG