ዋሺንግተን ዲሲ —
ሌሊሳ ዲሳሳ በቦስተኑ ማራቶን፥ ጥላሁን ረጋሳ በሮተርዳም ማራቶን፥ ቀነኒሳ በቀለ በታላቁ የአየርላንድ ሩጫና ኃይሌ ገብረሥላሴ በቪዬና ግማሽ ማራቶን ነው ትላንትናና ዛሬ ድል የተቀዳጁት። በሮተርዳሙ ማራቶን ሁለተኛ የወጣውም ኢትዮጵያዊ ነው። ጌቱ ፈለቀ ይባላል። በሴቶቹም ኢትዮጵያውኑ የሁለተኛ፥ አምስተኛና ስድስተኛነቱን ሥፍራ ወስደዋል። ሁለተኛዋ አበበች አፈወርቅ ናት።
በቦስተኑ 5 ኪሎ ሜትር ባለ ድሉ ደግሞ፥ ደጀን ገ፡መስቀል ሆኗል።
ደጀን በ 2012ቱ የለንደን ኦሊምፒክስ በ 5ሺህ የብር ሜዳልያ ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል።
በቦስተኑ 5 ኪሎ ሜትር ባለ ድሉ ደግሞ፥ ደጀን ገ፡መስቀል ሆኗል።
ደጀን በ 2012ቱ የለንደን ኦሊምፒክስ በ 5ሺህ የብር ሜዳልያ ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል።