በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


Bloomberg የዜና አገልግሎት ድረ-ገጽ ኢትዮጵያ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማጠናከር ስትል የመጀመርያ የኢንዱስትሪ ቀጠና ልትከፍት ነው ይላል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መኮንን ያዘዋል በተናገሩት መሰረት ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚላኩ እቃዎች መር የሆነውን የመጀመርያ የኢኮኖሚ ማእከል የምትከፍተው የኢኮኖሚው እድገት ለማፋጠን ነው።

የኢንዱስትሪው ማእከል የሚከፈተው እስከ ሰኔ ወር ማብቅያ ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሆነ አዲስ አበባ ውስጥ በሚመሰረተው ማእከል ስራ ለመጀመር ከመንግስት ጋር እየተነጋገሩ ካሉት ኩባንያዎች መካከል የደቡብ ኮርያ ልብስ አምራቾች እንደሚገኙባቸው ሚኒስትር መኮንን ማንያዘዋል እንደገለጹ ብሉምበርግ ጠቅሷል።

ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ የወጣ ጽሁ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት የመንደር ምስረታ በሚል መርሀ-ግብር እአአ በ 2010 አም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ለዘመናት ከኖሩባቸው መንደሮች እያፈናቀለ በሌሎች ቦታዎች አሰፈራቸው። አላማው በተለያየ ቦታ ተበታትነው የሚኖሩትን ሰዎች በመንደር አሰባስቦ ትምህርት ቤቶች፣ የህክምና ጣብያዎች፣ መንገዶችና ሌሎቾም መንግስታዊ አገልግሎቶች ወደ ሚገኙባቸው አከባቢዎች ቀርብ እንዲሉ የሚል ነው።

ይሁንና በመንደሮች የማሰባሰቡ መርሀ-ግብር ሰፋፊ መሬቶችን ለመዋዕለ-ነዋይ መዳቢዎች ለመስጠት ካለው እቅድ ጋር በተይያዘ በሰብአዊ መብት ረገጣ የተበከለ ሆኗል ሲል ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ የወጣው ጽሁፍ ዘግቧል።
AMH-af-Ethiopia-Press-Review-3-22-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:52 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG