በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጂሃዳዊ ሀራካት እና ወንጀል በፍርድ እስከሚጣራ ነጻ ሆኖ የመገመት መብት


በፌዴራላዊ መረጃ ደህንነትና በፌዴራል ፓሊስ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዚን ተዘጋጅቶ የተሰራጨዉ ጂሃዳዊ ሀረካት የተባለ ፊልም፣ በሽብር ተጠርጥረዉ እስር ቤት የሚገኙ የ29 የእስልምና እምነት ተከታዮች ፍርድ ሳይጠናቀቅ ለሕዝብ መቅረቡ በፍትህ የመዳኜት መብታተዉን ጥሷል ይላሉ ጠበቆቻቸዉና ደጋፊዎቻቸዉ።

እስረኞቹ ስቆቃና ድብደባ ደርሶባቸዉ ተገደዉ ከተናገሩት ዉጪ ፍልሙ እዉነትነት የሌለዉና የኢትዮጵያ ሙስልሞችን ጥያቄ ሆን ብሎ ከአንዳንድ የአፍሪቃ አሸባሪ ድርጅቶች ጋር ያገናኘ ነዉ፤ ስለዚህም አንድ ተጠርጣሪ የተከሰሰበት ጉዳይ በፍርድ ሂሰት እስከሚጣራ ከወንጀሉ ነጻ ሆኖ የመገመት መብት አለዉ የሚለዉን የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ ጥሷል ይላሉ ጠበቆቻቸዉ።

የፊልሙ አካላት አዘጋጆች የመንግስት ባለ ስልጣናት የፊልሙ አላማ በአፍሪቃ ቀንድ ያለዉን የአልቃይዳና የአልሸባብ ቡድኖች በኢትዮጵያ የተፈጠረዉን የሙስልሞች ጥያቄ እንደ ክፍተት በመጠቀም የተሳሳተና የእምነቱን ተከታዮች ወደ ጽንፈኝነት የሚያመራ አስተምሮት እንዳያስተምር፤

በሌሎቹ የአህጉሪቱ ክፍሎች የሚታየዉን የሽብርተኝነት እንቅስቃሴና በሰዉ ልጆች ህይወትና ንብረት ላይ እያደረሰ ያለዉን ከፍተኛ ጉዳት አስቀድሞ ለመከላከል ነዉ ብለዋል።

”የጥያቄዎ መልስ ዝግጅት“ በታሳሪዎቹ ፍትሃዊ ፍርድ ማግኜትና በአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዙሪያ ለቀረቡ የአድማጭ ጥያቄዎች የሕግ ባለሙያ መልስ ከአዲስ አበባ የህግ ባለሙያ አነጋግሮአል፣ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ይባላሉ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:31:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አስተያየቶችን ይዩ (26)

XS
SM
MD
LG