1/11/13 —
የ United States መንግስት ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ይሰጥ የነብረው ገንዘብ መቀነስ HIV ን በመታገል ረገድ ሀገሪቱ ያሳየችውን መሻሻል ሊጎዳ ይችላል ሲል IRIN የተባለው ስለ ሰብአዊ ጉዳዮች የሚዘግብና የሚተነትን የዜና አገልግሎት ጠቅሷል።
በአለም አቀፍ የጤና ፖሊሲ በስራ አስኪያጅነት የሚመሩት በአለም አቀፍ የልማት ማእከልም አንጋፍ አባል የሆኑት አማንዳ ግላስማን PEPFAR በሚል አህጽሮት በሚጠራው የ United States ፕረዚዳንት የአስቸኳይ ግዜ የ AIDSን ህመም የማቃለል እቅድ መሰረት ለኢትዮጵያ ይሰጥ የነበረው ገንዘብ በ 79 ከመቶ ሊቀነስ ይችላል ሲሉ ጽፈዋል።
የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች የገንዘቡ መቀነስ ያሳሰባቸው መሆኑን ቢገልጹም የምንጠብቀው ነገር ነው ማለታቸውን IRIN ጠቁሟል።
አንድ allAfrica.com ላይ የወጣ ጽሁፍ ደግሞ Sol Rebels ስለተባለው በኢትዮጵያ ስላለ የጫማ ፋብሪካ አፍላቂነትና ስኬት ዘግቧል። ይኸው የጫማ ፋብሪካ በያዝነው አመት በታይዋን ሁለተኛ የመሽጫ መደብር እንደሚከፍት አውስቷል።
የጫማ ው ፋብሪካ የማ ይፈለጉ ነገሮችን መልሶ እጥቅም ላይ በማዋል ምቹ ጫማዎች የሚያመርት ሲሆን የተለያዩ በአፍላቂነት ላይ የተመሰረቱ የጫማ አይነቶችን በ 55 ሃገሮች ይሸጣል። በኢትዮጵያ እየመጠቁ ከሄዱት የንግድ ተቋማት አንዱ ለመሆን በቅቷል ሲል allAfrica.com ላይ የወጣው ጽሁፍ ጠቁሟል።
npr ማለት National Public Radio የተባለው እውቅ ህዝባዊ ሬድዮ ጣብያም በአዲስ አበባ ስላለው የአህያ ማከምያ የጤና ጣብያ ዘግቧል።