በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሶቹ የኢትዮጵያ የስራ ዘርፎች



የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ደሳለኝ ሀይለማርያም
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ደሳለኝ ሀይለማርያም
የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ማህበራዊ ጉዳዮችን፣ መልካም አስተዳደርንና ሪፎርምን፣ ፋይናንስንና ኢኮኖሚን የሚመለከቱ ሶስት የስራ ዘርፎች እንደመሰረተይታወቃል።

ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንስቶ እስከ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕርግ ደረጃ የተሰየሙት ባለስልጣኖች ድረስ የስራ ድርሻቸው ተዘርዝሯል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የማህበራዊ ዘርፉን ይመራሉ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ቢሮን በሚኒስትርነት ማዕርግ ሲመሩ የነበሩት አቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእርግ የመልካም አስተዳደርና የሪፎርም ዘርፍን እንዲያስተዳድሩ የሲቪል ሰርቪስንም በሚኒስትርነት ማዕርግ እንዲያስተባብሩ

በቅርቡ የሕወሐት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ዶክተር ደብረ-ጽዮን ገ/ሚካኤል ከመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትርነታቸው በተጨማሪ የካቢኔውን የፋይናንስና የኢኮኖሚ ዘርፍ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕርግ እንዲከታተሉ ተሹመዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፓብሊሲቲ ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ጌታቸው ረዳ ስለ ዝርዝር ስራቸው ማብራርያ ሰጥተዋል። እንድታደምጡ እንጋብዛለን።
AMH-af-Ethiopia-New-Ministerial-Positions-1-5-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:20:02 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG