በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለሚደረግ ሰላማዊ ድርድር ዝግጁ ነኝ አለች፤ ኤርትራ ምንም አዲስ ነገር የለም ትላለች


ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም እና ፕሬዝደንት ኢሳያስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም እና ፕሬዝደንት ኢሳያስ
ሀገራቸው ሁሌም ለሰላም ድርድር ዝግጁ መሆኗን የገለጹት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፤ በኤርትራ በኩል ግን ተመሳሳይ ዝግጁነት አለመኖሩን ለፓርላማ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ሲናገሩ “ ከኤርትራ መንግስት ጋር ከለኝ ግንኙነት አንፃር የኢትዮጵያ ፖሊሲ ዛሬም አልተቀየረም፤ የኢትዮጵያ ፖሊሲ የዛሬ ስምንት አመት አካባቢ ያስቀመጥነው ፖሊሲ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ስምንት ነጥቦችን ይይዛል የተባለው ይህ ፖሊሲም በዋነኝነት የሰላም፤ የመልካም አስተዳደር፤ የመተሳሰብና የጋራ ልማትን ፍላጎትን የሚያንጸባርቅ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አቶ ሀይለማሪያም ባለፈው ወር ከአልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ከኤርትራው መሪ ጋር በማንኛውም ጊዜ ተገናኝተው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ምግለጻቸው ይታውሳል።
ይሄንን ተንተርሶ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለመንግስታቸው ልሳን ERITV ሲናገሩ፤ የሁለቱ ጎረቤት አገሮች ችግሮች አሁንም ያልተፈቱ መሆናቸውን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የመሪ ለውጥ መኖሩ ችግሩን እንደማይፈታው ገልጸው፤ ለውይይት የሚያበቃ መሰረት የለም ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንኑ ሲያብራሩ “ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አልፎ ሌላ በቦታው ስለተካ ችግሩ አይፈታም። በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቆዩት መሰረታዊ ልዩነቶችና ግጭቶች ምክንያት የራሱን ጥቅም ብቻ በሚያስቀድመው ጠባብ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው ቡድን እንዲሁም በተቀጥላነት በሚያገለግላቸው የውጭ ሃይሎች የተነሳ ነው። የዩናይትድ ስቴይትስ ጣልቃ ገብነትና የኢኮኖሚ ማእቀቦችም በችግሩ አካላት ናቸው።” ነበር ያሉት፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ እስካሁን ያልተፈታ የድንበር ይገባኛል ጥያቄ አላቸው። ከ1990-92 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ጦርነት ከሁለቱም ወገን ከ70ሽህ በላይ ዜጎች መገደላቸው ይገምታል።
ይሄንን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የይገባኛል ጥያቄ በተነሳባቸው የድንበር አካባቢዎች የሰላም አስከባሪ ሃይል እንዲያሰፍርና ገለልተኛ የአለም አቀፍ ሸንጎ፤ ድንበሩን እንዲያካልል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

የድንበር አካላይ ኮሚሽን ያሳለፈው ውሳኔ እስካሁን በአተረጓጎምና በተግባር ከማዋል አንጻር ሁለቱን አገሮች እያወዛገበ ይገኛል።
የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ ጋር ለመደራደር ኢትዮጵያ በሀይል ያዘችው ከሚሉት ግዛት መውጣት አለባት በማለት ይከራከራሉ። ፕሬዝደንት ኢሳያስ የህንኑ ሲያብራሩ
“ የአለም አቀፉ ድንበር አካላይ ኮሚሽን ያሳለፈውን ውሳኔ በመጣስ መሬታችንን ይዞ ከሚገኘው የአዲስ አበባ አስተዳድር ጋር ለድርድር የሚያበቃን የጋራ ጥቅም የለንም። አለም አቀፍ ድንበር አካላዩ ኮሚሽን የኤርትራን አቋም ይደግፋል።” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ እርስበርስ ተቃዋሚዎቻቸንው በማስታጠቅና በማደራጀት ይታወቃሉ። በሶማሊያ ውስጥም በእጅ አዙር አንዱ ከሌላኛው ወገር ጋር ይተነኳኮሳሉ በሚል፤ በተመሳሳይ ትችት ይሰነዘርባቸዋል።
የኢትዮጵያ መሪዎች በኤርትራ የሚሰለጥኑ ተቃዋሚዎች በሀገር ውስጥ ሰላም ለማደፍረስ ይሰራሉ በሚል ላቀረቡት ትችት ፕሬዝደንት ኢሳያስ በትግርኛ መልስ ሲሰጡ “በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ሁኔታ እንዴት እናነበዋለን?
ስለሚለው ለመናገር እንችላለን። የኢትዮጵያ ሁኔታ ምናልባት ጊዜ ሊወስድ፣ ስርአቱ በጠንካራ የአሜሪካ እንክብካቤ ስር ሆኖ እድሜውን ለማራዘም ይችል ይሆናል። ነገር ግን ኢትዮጵያ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ልትቀጥል አትችልም። ኢትዮጵያ ውስጥ ተቃውሞን የሚፈጥረው እዛው ያለው ስርአትና ፖለቲካ ነው።” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ ለአስርት ዓመታት ከቆየ የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ፤ በ1985ዓም በተካሄደ የህዝበ ውሳኔ ኤርትራ እራሷን የቻለች አገር በመሆን ነጻነቷን ማወጇ ይታወሳል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG