በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጧሪ ያጡ እናቶችን የቤት ባለቤት ያደረጉት የመቀሌ ባለሀብት


የአጥብያ ኮከብ - ሓጂ ዓብደላ ሓሰን
የአጥብያ ኮከብ - ሓጂ ዓብደላ ሓሰን
ሓጂ ዓብደላ ሓሰን በመቀሌ ከተማ የህንጻ መሳሪያዎች ነጋዴ ናቸው፡፡
እኚህ ግለሰብ ምንም ጧሪ ቤተሰብ ለሌላቸው 12 የመቀሌ ነዋሪ እናቶች ለያንዳንዳቸው መኖርያ ቤት ኣሰርተው ኣስረክበዋል፡፡ እያንዳንዱ ቤትም የራሱ መብራትና የውሃ ቆጣሪ፤ የገላ መታጠብያ፤ሽንት ቤት እና ኩሽና ቤት አለው፡፡


ሓጂ ዓብደላ ከዚህም በተጨማሪ መቀሌ በተለምዶ ቀበሌ 03 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩትን የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እንዳይቸገሩ በማሰብ መስጊድ ኣሰርተውላቸዋል፡፡ እንዲሁም በመስጊድ ቅጥር ግቢ ማህበረሰቡ የሚጠቀምበት የውሃ ጉድጓድና ለመስጊድ የአስተዳደር ስራ የሚያገለግሉ ተጨማሪ ክፍሎችን ሰርተዋል፡፡
“ይህንን የማደርገው የኣባቴን ኣደራ ለመጠበቅ ነው ፤ልጆቼም የኔን ፈር ይከተላሉ ብዬ ኣምናለሁኝ” ይላሉ ሓጂ ዓብደላ፡፡


ላለፉት 40 ኣመታት የቆየውን የአባታቸውንም ፈለግ ተከትለውም በመቀሌ ማረምያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎችን በረመዳን ጾም ከቤት ምግብ እያዘጋጁ ያቀርቡላቸዋል፡፡


ኣባታቸው ሓሰን ሳላሕ ባድረግም በመቀሌ በቀበሌ 8 እና 14 ለሚገኙ ኗሪዎች የ60 ሜትር ርዝመት ያለዉ ድልድይ ሰርተው እንደነበር ይነገርላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ማይጨው ከተማ ውስጥ የሚገኝውን መስጊድም የሰሩት አባታቸው እንደሆኑ ሓጂ ዓብደላ ያስረዳሉ፡፡

የሓጂ ዓብደላ የወደፊት ህልም ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ሆስፒታል መገንባት ነው፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG