1/4/13 —
Sudan Vision የተባለው እለታዊ እትም ድረ ገጽ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በሚቆጣጠሩትና ወጪውንም ሶስቱ ሃገሮች በሚሸፍኑት መንገድ መገንባት አለባት ሲሉ የሱዳን ጠብበት ጥሪ ማቅረባቸውን ዘግቧል።
ጠበብቱ ይህን ያሉት “ህዳሴ ግድብ በሱዳንና በግብጽ ላይ የሚኖረውአንደምታ” በሚል ርእስ ዋናው መሰረቱ ኻርቱም የሆነውInernational University of Africa ማለት አለም አቀፍ የአፍሪቃ ዩኒቨርሲቲ ኻርቱም ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በቅርቡ ባካሄዱት ሲምፖዝየም እንደሆነ ድረ-ገጹ ጠቅሷል።
በሌላ ዜና ደግሞ IndepthAfrica የተባለው ስለ አፍሪቃ ጉዳይ የሚዘግብ ድረ ገጽ ባቀረበው ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የምትልከው የመብራት ሃይል ሽያጭ ዋጋ ከሱዳን ከምታስገባው ነዳጅ ዘይት ጋር የሚመጣጠን እንዲሆን ለማድረግ ሁለቱ ሀገሮች እየተደራደሩ እንደሆነ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
እነዚህ ዘገባዎች የዛሬው ኢትዮጵያ በጋዜጦች ቅንብራችን ካካተታቸው መካክል ናቸው። እንድታደምጡ እንጋብዛለን።