በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


Ambassador Seyoum Mesfin
Ambassador Seyoum Mesfin
CHINADAILY የተባለ ድረ-ገጽ ኢትዮጵያ የቻይና ፋብሪካዎች መበራከትን እደምትጠብቅ ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ በሚደረገው የንግድ ስራ የቻይና የመዋእለ-ነዋይ አፍሳሾች የሚከተሉት አይነት በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት ፖሊሲ እንደሚመረጥ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ስዩም መስፍን አስገንዝበዋል።

አምባሳደር ስዩም መስፍን ቀጥለዋም “ቻይና በመሰረተ-ልማት ግንባታ ረገድ ዋናዋ ለጋሻችን፣ ትልቅ ገንቢና ዋናዋ የቴክኖሎጂ አቅራቢያችን ነች ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ቻይና ለወደፊቱ በኢትዮጵያ ዋና የፋብሪካዎች ባለቤትና በኢትዮጵያ ለሚመረቱ ምርቶች ትልቅ ገበያ ትሆናለች" ሲሉ አብራርተዋል ይላል CHINADAILY ድረ-ገጽ።

IRIN የተባለው ስለ ሰብአዊ ጉዳይ ዜናና ትንተና የሚያቀርብ የዜና አገልግሎት ደግሞ ወደ የመን ካደረገው አደገኛ ጉዞ በህይወት ተርፎ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ስለተደረገ አንድ ወጣት ዘግቧል።

ጀማል አህመድ የተባለ የ 21 አመት ወጣት በሳውዲ አረብያ ሄዶ በመስራት ከድህነት ለመውጣት እንዲችል ህገወጥ በሆነ መንገድ የመን በመግባቱ ለ 9 ወራት ያህል በእስር ከቆየ በኋላ መልሰው ወደ ሀገሩ እንደላኩት መናገሩን IRIN ጠቁሟል።
AMH-af-Ethiopia-Press-Review-12-28-12
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:51 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG