በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመን ለመጓዝ በጀልባ ተሳፍረው የነበሩ ኢትዮጵያዊያንና ሶማሊያዊያን በባህር ላይ ሰመጡ


የኢትዮጵያዊያንና ሶማሊያዊያን የባህር ላይ ጉዞ ወደ የመን
የኢትዮጵያዊያንና ሶማሊያዊያን የባህር ላይ ጉዞ ወደ የመን
ሰሞኑን ከሶማሊያ የባሕር ጠረፍ ተነስታ ስትቀዝፍ በነበረች አንዲት ጀልባ ላይ ተሣፍረው ከነበሩ ሰዎች መካከል 55ቱ የደረሱበት መጥፋቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር አስታወቀ፡፡

ጀልባይቱ ከመጠን በላይ ሰው አጨናንቃ አሣፍራ እንደነበረና ከፑንትላንዷ የወደብ ከተማ ከቦሣሶ ተነስታ 15 ደቂቃ ያህል እንደተጓዘች መገልበጧን ኮሚሽነሩ አክሎ አመልክቷል፡፡

ጀልባይቱ ስትነሣ የአየሩ ሁኔታ የተበላሸ እንደነበረ የአካባቢው ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን ይህ ምናልባትም ለአደጋው ምክንያት የሆነው ይኸው ሁኔታ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

ለጉዳቱ ከተጋለጡት ውስጥ የበዙት የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያዊያንና የሶማሊያ ዜጎችም የሚገኙ ሲሆን ለድብቅ አስተላላፊዎች ከፍለው በአደን ባሕረ ሠላጤ አቋርጠው ወደ የመን ለመሄድ እየተጓዙ እንደነበር ታውቋል፡፡
ከሥፍራው የሚወጡት ዘገባዎች የተለያዩ መረጃዎችን የያዙ ቢሆኑም ከአደጋው የተረፉና አሁን ተደብቀው የሚገኙ ሁለት ሰዎች ለቪኦኤ የኦሮምኛ ዝግጅት ክፍል በሰጡት መግለጫ ብዙ ገንዘብ በከፈሏቸው ሕገወጦቹ አስተላላፊዎቻቸው መደብደባቸውን አመልክተዋል፡፡

ሁለቱ ተጓዦች አብረዋቸው ካሉ የአደጋው ተጠቂዎች ከሆኑ አሥር የኦሮሞ ልጆች መካከል የሚገኙ ሲሆን እስከአሁንም ተይዘን ልንመለስ እንችላለን በሚል ሥጋት የሕክምና እርዳታ ለመጠየቅ አለመድፈራቸውን ተናግረዋል፡፡
XS
SM
MD
LG