በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጂቡቲ ኢትዮጵያ የምትገለገልበት የታጁራ ወደብ ግንባታ መሰረተ-ዲንጋይ ተጣለ


ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ
ጂቡቲ ውስጥ ታጁራ የተባለ በአብዛኛው ኢትዮጵያ የምትጠቀምበት አዲስ ወደብ እየተሰራ ነው። ክቡር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለ-ማርያም ደሳለኝ ከፍተኛ መልእክተኞችን መርተው ወደቡን ለመገንባት መሰረተ ልማት በመጣል ስነ-ስር አት ላይ ለመገኘት ጂቡቲ እንደሄዱ ተዘግቧል። ከወደቡ ወደ አፋር፣ አማራና ትግራይ ክልሎች የሚያመራ የባቡር ሀዲድ ይሰራል።

ኬንያ ውስጥም ከኢትዮጵያና ከደቡብ ሱዳን ጋር በመተባበር በአንድ ጊዜ 32 መርከቦችን ሊያስተናግድ የሚችል ትልቅ ወደብ እየተገነባ ነው። በተለይም ደቡባዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ኬንያ በዚህ ወደብ በመጠቀም እድገታቸውን ሊያራምዱ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ለአጎራባች ሀገሮች የኤለክትሪክ ሃይል የመላክ ትልቅ እቅድ እንዳልትም ይታወቃል። የምስራቅ አፍሪቃ የኤለክትሪክ ጎዳና የተባለው በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል የሚዘረጋው የኤለክትሪክ ማከፋፈያ መስመርም ውሎ አድሮ አምስት የምስራቅ አፍሪቃ ሀገሮች ይገለገሉበታል ተብሏል።

የአፍሪቃ ጉዳይ ምሁር ዶክተር አየለ በከሬ እንዲህ አይነቱ የአጎራባች ሀገሮች ትብብር ስለሚኖረው ጥቅም ተንትነዋል። እንድታደምጡ እንጋብዛለን።
AMH-af-AT-Ethiopia-Dijibouti-Tadjura-port-12-17-12
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:30 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG