በአይነቱ የተለየና ገንዘብ ቆጣቢ የወር አበባ መቀበያ ማምረቻ ፋብሪካ በመቀሌ ከተማ ተቋቋመ፡፡ በ2002 ዓ.ም የተቋቋመው “ማርያም ሰባ የንጽህና ምርቶች ማምረቻ” የተባለው ይህ ድርጅት እየታጠበ ለኣንድ
ኣመት የሚያገለግል የወር ኣበባ መቀበያ ጨርቅ ወይም ሞዴስ (Reusable Sanitary Pads) እያመረተ በማከፋፈል ላይ ይገኛል፡፡
እንደ ድርጅቱ ባለቤት ወ/ሮ ፍረወይኒ መሰረት ፋብሪካው በዓመት መታጠብ የሚችል 100 ሽህ የወር አበባ መቀበያ ያመርታሉ፡፡ ድርጅቱ ለዚሁ የፈጠራ ውጤት ከኢትዮጵያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት የባለቤትነት ማረጋገጫ ማግኘቱን ወ/ሮ ፍረወይኒ ገልፀዋል፡፡