በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት፤ በአዲሱ የኢትዮጵያ ካቢኔ አሿሿም ዙሪያ


የኢትዮጵያ ካቢኔ አሿሿም
የኢትዮጵያ ካቢኔ አሿሿም
ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በቅርቡ ከምክትላቸዉ አቶ ደመቀ መኮንን በተጨማሪ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማእረግ ሁለት ባለሥልጣናት መሾማቸዉ ይታወሳል።

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ደብረ ጽዮን-ገብረ ሚካኤል በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት ማእረግ የንግድና ፋይናንስ “ክለስተር” አስተባባሪ እንዲሆኑ፤ እንዲሁም አቶ ሙክታር ከድር በምክርት ጠቅላይ ሚንስትርነት ማእረግ የመልካም አስተዳዳር ለዉጥ አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚንስትርም ሆነዉ ተሹመዋል።

የኢትዮጵያ ፓለቲካ ተቃዋሚ መሪዎችና አንዳንድ ገምጋሚዎች፤ “ህገ-መንግስቱ ከአንድ በላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሰለማይፈቅድ ህገወጥ ነዉ፤” ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ “በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት ማእረግ” እና “የክላስተር-መሪ” የሚሉት ቅጥያ ሥያሜዎች ላይ በማስመር “ከአንድ በላይ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አልተሾመም፤” በማለት ይከራከራሉ።

እነኚህን ተቃዋሚ እይታዎች ለመቃኘት ሁለት ጋዜጠኞችና አንድ የሕግ ባለ ሞያ ጋብዘናል። የአዲስ ፎርቹንጋዜጣ ማኔጂግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረ-ጊዮርጊስ፤ የቀድሞ የፍትህ ጋዜጣ የቀድሞ ዋና አዘጋጅና አሁን የአዲስ ታይምስ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ደሳለኝና እንዲሁም የሹመት አሰጣጡን ከአገሪቱ ህኅገ-መንግስት አንጻር የሚተነትኑልን የህግ ባለሙያው አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ናቸው።

ኅገ መንግስትና የመንግስት የሥልጣን ገደብ፤ እንዲሁም የአገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ በውይይቱ ትኩረት ከሚደረግባቸው አበይት ጭብጦች ውስጥ ናቸው።ሙሉ ውይይቱን ቀጥሎ ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:16:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


please wait

No media source currently available

0:00 0:23:23 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG