በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት፤ በአዲሱ የኢትዮጵያ ካቢኔ አሿሿም ዙሪያ


የኢትዮጵያ ካቢኔ አሿሿም
የኢትዮጵያ ካቢኔ አሿሿም
ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በቅርቡ ከምክትላቸዉ አቶ ደመቀ መኮንን በተጨማሪ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማእረግ ሁለት ባለሥልጣናት መሾማቸዉ ይታወሳል።


የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ደብረ ጽዮን-ገብረ ሚካኤል በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት ማእረግ የንግድና ፋይናንስ “ክለስተር” አስተባባሪ እንዲሆኑ፤ እንዲሁም አቶ ሙክታር ከድር በምክርት ጠቅላይ ሚንስትርነት ማእረግ የመልካም አስተዳዳር ለዉጥ አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚንስትርም ሆነዉ ተሹመዋል።


የኢትዮጵያ ፓለቲካ ተቃዋሚ መሪዎችና አንዳንድ ገምጋሚዎች፤ “ህገ-መንግስቱ ከአንድ በላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሰለማይፈቅድ ህገ ወጥ ነዉ፤” ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ “በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት ማእረግ” እና “የክላስተር-መሪ” የሚሉት ቅጥያ ሥያሜዎች ላይ በማስመር “ከአንድ በላይ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አልተሾመም፤” በማለት ይከራከራሉ።


ይህን ተጻራሪ አመለካከት እንዲያብራሩልን ሁለት ጋዜጠኞች ጋብዘናል። የአዲስ ፎርቹንጋዜጣ ማኔጂግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረ-ጊዮርጊስ፤ የቀድሞ የፍትህ ጋዜጣ የቀድሞ ዋና አዘጋጅና አሁን የአዲስ ታይምስ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ደሳለኝና እንዲሁም የህግ ባለሙያው አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ከአገሪቱ ህኅገ-መንግስት አንጻር የሹመት አሰጣጡን ይተነትኑልናል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:16:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG