በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ
አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ
የዐል ጂዚራ የዜና አውታር በገለጸው መሰረት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ካስፈለገ አስመራ ድረስ ሄደው ከፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቁ ጋር የሰላም ድረድር ለማደረግ ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከዐልጄዚራ ጋር ባደረጉት በመጪው ቅዳሜ በሚተላለፍ ቃለ ምልልስ እንደሆነ ድረ-ገጹ ጠቁሟል። ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለመነጋገር ያላት ፍላጎት የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፖሲን በመከተል እንደሆነ የተናገሩት የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አስማራ ድረስ ሄደው ሳይቀር ከፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለመደራደር ከ 50 ጊዜ በላይ ጠይቀዋል ሲሉ እንዳስገነዘቡ ዐል ጂዚራ ድረ-ገጽ ጠቅሷል።

ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ደግሞ ኤርትራ ለአፍሪቃ ብሄራዊ ሻምፕዮና የማጣርያ ውድድር ከኢትዮጵይ ጋር እንድታካሄድ ተመድቦ ከነበረው የአፍሪቃ ሻምፕዮና የማጣርያ የእግር ኳስ ውድድር እንደወጣች ከአፍሪቃ የእግር ኳስ ኮንፈደረሽን የቀረበ ደብዳቤ ማመልከቱን ገልጿል።

ሌሎችም ርእሶች ይገኙብታል እንድታደምጡ እንጋብዛለን።
AMH-af-Ethipia-Press-Review-12-7-12
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:37 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG